አዲስ መጽሐፍ
የመምህርነት ሙያ እና የትምህርት ጥራት በኢትዮጵያ
ከሙያ-አልባ መምህር ወደ መምህር-አልባ ክፍል ወይስ?
አክሊሉ ዳለሎ (ፕሮፌሰር)
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ፣ የመምህራን ትምህርት ክፍል
As Featured On



የቀዳሚ አንባቢያን አስተያየት
ይህ መጽሐፍ… ለመምህርነት ሙያ የፖሊሲ ግብዓት በመሆን፣ መሠረታዊና ዘለቄታ ያለው ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችልና፣ ለአገራችንም ብሩህ ተስፋ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“… ትኩረት ለተነፈገው ሙያ ትኩረትን፣ ለአንባቢያን በስነትምህርት ሳይንስ ጠብሰቅ ያለ እውቀትን፤ በዘርፉ ላሉ ምሁራን ከተምሳሌትነት በተጨማሪ የማጣቀሻ ጽሁፍ አግልግሎትንና ለማህበረሰቡና ለመንግስት ደግሞ አገርን ለመታደግ የማንቂያ ደወል የመሆን አገልግሎት እንዲሰጥ ስለመዘጋጀቱ ረቂቁን ሳነብ በደንብ ተረድቻለሁ፡፡”
ፕሮፌሰር በላይ ተፈራ
አዲስ አበባ ዩኒቨርnሲቲ
“የትምህርት ባለሙያዎች፣ በታሪክ አጋጣሚ ያለበቂ ልምድና የትምህርት ዝግጅት በየደረጃው የትምህርት ስርዓቱን እየመሩ ያሉ፣ እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ይሄንን መጽሐፍ ቢያነቡ እንደሚጠቀሙ ላስገነዝብ እወዳለሁ፡፡ በትምህርት ስርዓቱ ስለሚታየው ውድቀትና ውዥንብር መንፈሳዊ ህመም የሚሰማቸው ሁሉ መጽሐፉን እንዲያነቡ እመክራለሁ፡፡”
ፕሮፌሰር አምብሳ ቀነአ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“በትምህርትና በአጠቃላይ ሀገራዊ ልማት ላይ አትኩረው የሚመራመሩ ምሁራን፤ በቅደመ-ምረቃና በድህረ-ምረቃ ደረጃ ላሉ ተመራማሪዎች እንዲሁም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ ነው፡፡”
ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሰመላ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
“… ከፍተኛ ልብ አንጠልጣይ ግርምትን የሚጭሩ፤ የሚያስደንቁ በአንፃሩ ደግሞ እጅግ የሚያሳዝኑ፤ የሚያስደምሙ የመምህርነትና መምህራን አገርአቀፍና ዓለምአቀፍ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው፡፡ ምናልባትም እኔ በሙያው ውስጥ ስላለሁ ነው መሰለኝ በታሪኩ በጣም ልቤ ተነክቷል፡፡”
ዶ/ር ሐረገወይን ፋንታሁን
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያን የመምህራን ሙያና የመምህራን አሠለጣጠን በተለየ አቀራረብና በድፍረት ፍንትው አድርጎ በአገራዊ ቋንቋ
በማቅረቡ በአይነቱ የተለየ ምናልባትም የመጀመሪያው ሊያደርገው ይችላል፡፡”
ዶ/ር ሰለሞን አርአያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ የመምህርነት ሙያና የትምህርት ጥራት ላይ በተጠናከረ ጥናት የተመሠረተ የመጀመሪያው መጽሐፍ ነው፡፡”
ዶ/ ር መስፍን ሞላ ደምሴ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
“… ይኸን መጽሐፍ በማንበባችሁ የመምህርነት ሙያ በኢትዮጵያ ከየት ወደ የት ለሚለው ጥያቄያችሁ ትክክለኛ ምላሽ ልታገኙ
እንደምትችሉ ከፍተኛ ግምት አለኝ።”
ፕሮፌሰር ሰሎሞን መለሰ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
“ይህ መጽሐፍ ከአፀደ ህፃናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ላለው ተማሪና መምህር ምርጥና ድንቅ ትምህርት ቤት ሆኖ አግኝቻለሁ:: …
ለመምህርነት ሙያ ክብር፣ ለመምህራን ብቃትና ክህሎት፣ እና ለትምህርት ጥራትና ለአገር እድገት ችግሮች ዝርዝር የመፍትሔ ምክረ-
ሃሳቦችን አቅርቧል:: ሁሉም ያድምጥ!”
ፕሮፌሰር ተሰማ ኤርሱሞ
ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“ባጭሩም፣ ይህ የፕሮፌሰር አክሊሉ መጽሐፍ ሰሚ ሳይሆን አድማጭ ጆሮዎችን አግኝቶ ወደተግባር ከተመነዘረ፣ ለእኔ፡- ስም፣ ታይትል፣
ሞያ፣ ልምድ እና አገራዊ ስሜት ህብር “Harmony” ፈጥረው የተጣመቁበት ተምሳሌታዊ የትምህርት ጥም ማርኪያና የአገራዊ እድገት
ፍኖት ተላሚ ሥራ እንደሆነ አምናለሁ፡፡”
ዶ/ር ዳዊት አዲሱ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“ይህንን መጽሐፍ ካነበባችሁ በኋላ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ ህብረተሰቡ፣ የትምህርት ቤት ኃላፊዎችና መንግሥት ትኩረት
በመስጠት የመምህራንን ህይወትና በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ላይ የአቅማችሁን አስተዋፅኦ ታደርጋላችሁ ተብሎ ይጠበቃል።”
ፕሮፌሰር ሙሉጌታ አጥናፉ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
“አገራችንን እየመሩ ያሉ ትላልቅ ባለስልጣናት እና ምሁራን ጭምር ይህን መጽሐፍ አንብበው ከገጠመን የትምህርት ቀውስ እንድንወጣ
የድርሻችንን ለመወጣት የዕቅድ መነሻ ይሆናል ብየ አምናለሁ፡፡”
ሽመልስ አበበ
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር (ኢመማ) ም/ ፕሬዚዳንት